ቀጥታ፡

19ኛው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በደቡብ ወሎ ዞን አርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ መዲና ከተማ እየተከበረ ነው

ደሴ፤ ህዳር 8/2017(ኢዜአ)፦19ኛው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በደቡብ ወሎ ዞን አርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ መዲና ከተማ እየተከበረ ነው።

በዓሉ እየተከበረ ያለው "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ ሲሆን በበዓሉ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላትና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አህመድ ኑሩ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት ህገ-መንግሥቱ የአርጎባን ብሄረሰብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት አጎናጽፏል።


 

በዚህም ብሄረሰቡ በራሱ ቋንቋና ባህል የልማትና የሰላም ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸው የአርጎባ ቋንቋን ለመጠበቅና ለማስፋፋት የሚያስችሉ ተግባራትም እየተከናወኑ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

በወረዳው ህብረተሰቡን በማስተባበር ሰላሙን ከመጠቅ ባለፈ የተለያዩ ልማቶች እየተሰሩ እንደሆነም ተናግረዋል።

በበዓል አከባበሩ በክልሉ የተለያዩ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች አመራር አባላት በተጨማሪም ከአፋር ክልል የተወከሉ አካላትም እየተሳተፉ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም