ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት የምትመራውና በከባቢ አየር ላይ ያተኮረ የአፍሪካ ሚኒስትሮች ኮንፍረንስ በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት የምትመራውና በከባቢ አየር ላይ ያተኮረ የአፍሪካ ሚኒስትሮች ኮንፈረንስ በአዘርባጃን ባኩ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ከ29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ(ኮፕ 29) ጎን ለጎን እየተካሄደ ያለውን ኮንፈረንስ በፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) ሊቀመንበርነት የሚመራ ነው።

በኮንፈረንሱ ላይ የአፍሪካ ሚኒስትሮች፣ባለሙያዎች እና የልማት አጋሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

በኮንፈረንሱ ቁልፍ በሆኑ የከባቢ አየር ጉዳዮች፣ የአየር ንብረት ለውጥ ድርድሮች እና የአፍሪካ የዘላቂ ልማት ዋንኛ ትኩረቶች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተደራዳሪ ቡድን ስራዎች፣ አፍሪካውያን በአየር ንብረት ለውጥ እና በሳይንስ ምርምር ያላቸው ሚና እና በቀጣይ በሚካሄደው 20ኛው የአፍሪካ ሚኒስትሮች የከባቢ አየር ኮንፈረንስ ላይ የውይይቱ አጀንዳዎች መሆናቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም