የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን አገኘ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 7/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለሁለተኛ ተከታታይ ግዜ በ “Arabian Cargo Awards” ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን ተቀዳጀ።
የሽልማት አሰጣጥ መርሐግብሩ በዱባይ ከተማ መካሄዱንና በገልፍ ሀገራት ለሚሰጡ ምርጥ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎቶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ እንደሆነም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።