በአፋር ክልል 19ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል - ኢዜአ አማርኛ
በአፋር ክልል 19ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል
ሰመራ፤ ህዳር 6/2017(ኢዜአ)፦ በአፋር ክልል 19ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ምክር ቤት አስታወቀ።
ከክልሉ ከተለያዮ ወረዳዎች የተውጣጡ አፈ ጉባዔዎች በተገኙበት የበዓሉን አከባበር በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የአፋር ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወ/ሮ መይረም መሐመድ እንደገለጹት የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ኢትዮጵያውያን ህብረታቸውን አጉልተው የሚያሳዩበት ነው።
"ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ደምቆ የሚታይበትና አንድነታችንን አጠናክረን የምናሳይበት ነው" ብለዋል።
19ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ስናከብር የጋራ የሆኑ መገለጫዎቻችንን በማድመቅ ነው ሲሉም አክለዋል።
እኩልነትን በማስፈንና አብሮነትን በማስቀጠል ረገድ በዓሉ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው በዓሉ በተለያዮ ወረዳዎች በድምቀት እንደሚከበር አመላክተዋል ።
ወንድማማችነት የሚጠናከርበት የብሄር ብሄረሶችና ህዝቦች ቀን በአል አንድነት የሚደምቅበት መሆኑን ጠቅሰው በአፋር ክልል ደረጃ የተገኙ የልማት ውጤቶች የሚታዩበት እና የሚጎበኙበት መሆኑን አስረድተዋል።
ህገ መንግስቱ ያስገኛቸውን ትሩፋቶችን ማክበርና ማስጠቀጠል እንደሚገባ ወ/ሮ መይረም አስገንዝበዋል።