ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ከሆኑት ማርያም ሳሊም ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ከሆኑት ማርያም ሳሊም ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 6/2017(ኢዜአ)፦ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ከሆኑት ማርያም ሳሊም ጋር ተወያይተዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፥ የዓለም ባንክ በከተማ አስተዳደራችን በሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ፣ በአቅም ግንባታ፣ በተማሪዎች ምገባ፣ በትራንስፖርትና መንገድ ዘርፍ እንዲሁም በውሃና ፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም ፥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተሰራ ያለውን ስራ ከጐበኙ በኋላ ይበልጥ ለመደገፍ የሚያስችል ውይይት አካሂደናል ብለዋል።