ቀጥታ፡

የዓለም ሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባኤ በግንቦት ወር በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2017(ኢዜአ)፦ 20ኛው የዓለም ሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባኤ ከግንቦት 11 እስከ 15/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ጉባኤውን አስመልክተው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና የዓለም ሥራ ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ተወካይ ኑዋላ ካምባላ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚሁ ወቅት ጉባኤው "በአስቸጋሪ ዓለም ተለዋዋጭ ሁኔታን መቋቋም የሚችል ማህበረሰብ መፍጠር" በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

ጉባኤው ከግንቦት 11 እስከ 15/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚካሄድ ጠቁመው ዘርፉን የሚዳስሱ ጥናታዊ ጹሁፎች እንደሚቀርቡበት አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም ተሳታፊዎቹ በኢትዮጵያ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙም ተናግረዋል።

በጉባዔው ፖሊሲ አውጪዎች፣ የአሰሪዎች እና የሰራተኞች ማህበራት እና ሰራተኛ-ተኮር የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የአካዳሚክ እና የምርምር ተቋማት እንደሚሳተፉ ጠቅሰዋል።

ጉባኤውን በስኬት ለማከናወን ከ15 የመንግሥት ተቋማት የተውጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ሚኒስትሯ አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም