ቀጥታ፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል አለበት-አምባሳደር እጸገነት በዛብህ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 4/2017(ኢዜአ)፦ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር እጸገነት በዛብህ አሳሰቡ።

በኡጋንዳ ካምፓላ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ብሔር ክፍሌ ለሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ የ31 ሺህ 425 የአሜሪካን ዶላር ቦንድ ግዢ ፈጽመዋል።

ወይዘሮ ብሔር ካምፓላ ኤምባሲ ተገኝተው የቦንድ ግዢውን የፈፀሙ ሲሆን የቦንዱን ሰነድ በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር እጸገነት በዛብህ ይመኑ እጅ ተረክበዋል።

አምባሳደር እጸገነት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሀገራችን ኩራት መሆኑን ገልጸው፥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ግድቡ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሚያደርገውን ርብርብ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

ወይዘሮ ብሔር እና ቤተሰቦቻቸው የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከዳር እንዲደርስ በተደጋጋሚ እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የቦንድ ግዢውን የፈጹመት ወይዘሮ ብሔር ክፍሌ በበኩላቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ሀገራዊ ፕሮጀክት መሆኑን አንስተዋል።

ግድቡ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም