ቀጥታ፡

በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንሰራለን - ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 3/2017(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንሰራለን ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼይ ሀይን ጋር ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት በሁኔታዎች የማይለወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት መድረሱን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ይህን ጠንካራ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ በውይይታቸው ላይ ገልጸዋል።


 

የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በአፍሪካ ቻይና የትብብር መድረክ(ፎካክ) ማዕቀፍ ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ለመተግበር እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያም ለአምባሳደሩ ገለጻ መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በሁለትዮሽ ብቻ ሳይሆን በባለብዙ ወገን ግንኙነት በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ በጋራ እንደምትሰራ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የሕዝባዊት ሪፐብሊክ ቻይና አምባሳደር ቼይ ሀይ በፎካክ ጉባዔ ላይ የሁለቱ አገራት መሪዎች መግባባት ላይ የደረሱባቸውን የኢኮኖሚ፣ንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም