ቀጥታ፡

የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጣና በሙሉ አቅሙ ወደ ተሟላ ትግበራ ገብቷል - ፍስሃ ይታገሱ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ህዳር 3/2017(ኢዜአ)፦የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጣና በሙሉ አቅሙ ወደ ተሟላ ትግበራ መግባቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ(ዶ/ር) ገለጹ።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህን የገለጹት በነጻ ንግድ ቀጣናው ስራ ለመጀመር ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢንቨስትመንት ፍቃድ በማውጣት ሂደት ላይ ያሉ ባለሀብቶች ነጻ ንግድ ቀጣናው እየሰጠ ያለውን አገልግሎት በጎበኙበት ወቅት ነው።

ነጻ ንግድ ቀጣናውን ወደ ተሟላ ትግበራ ለማስገባት የሚያስችሉ ስራዎች ባለፉት ሶስት ወራት በባለድርሻ አካላት በልዩ ትኩረት ሲሰሩ መቆየታቸውም ተገልጿል።


 

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ባለሀብቶቹ ወደ ነጻ ንግድ ቀጣናው ገብተው ስራቸውን እንዲጀምሩ የሚያስችሉ ድጋፎች በሙሉ እንደሚደረጉ ገልጸው የዛሬው ጉብኝትም የዚሁ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመንግስት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ ሀገር አቀፍ የነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ ኮሚቴ የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣናን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ በመገምገም ነጻ ንግድ ቀጣናው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ተገቢውን ርብርብ ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል።

የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያሰተዳድራቸው ፓርኮች ውስጥ ወደ ነጻ ንግድ ቀጣናነት በማደግ የመጀመሪያው ሲሆን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች ምርታቸወን ለገበያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙም ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም