ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።

የሩሲያ- አፍሪካ የትብብር ፎረም የመጀመሪያው የሚኒስትሮች ጉባዔ በሩሲያ ሶቺ ከተማ ዛሬ ይጀመራል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ከጉባዔው አስቀድሞ ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተወያይተዋል።


 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።

በውይይታቸውም የኢትዮጵያ እና ሩሲያን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ለማጎልበት እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን የሚያሳድጉ እምቅ አቅሞችን ለመጠቀም ተስማምተዋል።

የሩሲያ-አፍሪካ የትብብር ፎረም የመጀመሪያው የሚኒስትሮች ጉባዔ ዛሬ እና ነገ በሩሲያ ሶቺ ከተማ እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም