የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚና የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የወልወል ድህረ-ምረቃ እና የ25ኛ ሰላም ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚና የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የወልወል ድህረ-ምረቃ እና የ25ኛ ሰላም ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚና የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የወልወል ድህረ-ምረቃ እና የ25ኛ ሰላም ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ይገኛል።
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ ጄኔራል መኮንኖችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ተመራቂ ዕጩ መኮንኖች በማሠልጠኛ ማዕከሉ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩና የሚጠበቅባቸውን ሥልጠና ወሥደው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተጠቁሟል።
ተመራቂዎች በእውቀት፣ በክህሎት እና በአስተሳሰብ ሙሉ የሚያደርጋቸውን የመሪነት ስልጠና የወሰዱ መሆኑ ተገልጿል።