ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በጎንደር ከተማ የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ - ኢዜአ አማርኛ
ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በጎንደር ከተማ የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2017(ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በጎንደር ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኙ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ።
የመንግስት የስራ ኃላፊዎቹ ጎንደር ከተማ አፄ ቴዎድሮ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘውና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በቆይታቸውም በፌደራልና በክልሉ መንግስት ትብብር በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ይጎበኛሉ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር ሰጭነት በጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት፣ የጎንደር አዘዞ የ12 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ፣ የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስት ዕድሳት፣ የመገጭ ግድብ ግንባታን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የልማት ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።