የሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮ እና የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮ እና የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2017(ኢዜአ)፦ የሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮ እና የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ጎበኙ።
ለሁለቱ ሀገራት መሪዎች የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በጉብኝቱ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ፣ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና የአየር ኃይሉ አመራሮች ተገኝተዋል።
አገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግሥት ለፀጥታና ደህንነት ተቋማት ሪፎርም በሰጠው ትኩረት የኢትዮጵያን ከፍታ የሚመጥንና ትውልድ የሚያኮራ አየር ኃይል መገንባቱ ለመሪዎቹ ተገልጾላቸዋል።
መሪዎቹ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰው ኃይል፣ በትጥቅና ምቹ የሥራ ከባቢ ያደረጋቸውን ሪፎርሞች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
አየር ኃይሉ በምስረታው በአፍሪካ ቀደምት ታሪክ ያለው መሆኑም ይታወቃል።