ቀጥታ፡

ረሃብን መዋጋት የጋራ ምላሽን ይሻል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2017(ኢዜአ)፦ ረሃብን መዋጋት የጋራ ምላሽን ይሻል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ረሃብን መዋጋት የጋራ ምላሽን ይሻል ብለዋል።

ለዚህም ለምግብ ዋስትና የሚሆን የአለም አቀፍ ድጋፍ አቅርቦት፣ ድንበር ዘለል የሆነ የእውቀት ማካፈል ልምምድ፣ ለፍትሃዊ ተደራሽነት የሚረዳ የፖሊሲ መናበብ ብሎም ለሴቶች ትኩረት የሚሰጥ የአነስተኛ አርሶና አርብቶ አደሮች ድጋፍ ሥራ አስፈላጊ ነው ሲሉም ገልጸዋል።


 

የ’World Without Hunger’ ጉባኤን ስናጠናቅቅ፣ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ውይይቶች የተሳኩ ይሆኑ ዘንድ አስተዋፅዖ ያበረከቱትን ተሳታፊዎች ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው።

አርባ ቢሊዮን ዛፎች በተተከሉበት ምርታማነትን በሚያሳድጉ የለውጥ ሥራዎች፣ ድርቅን በሚቋቋሙ አዝርዕት ልማት፣ በ #አረንጓዴዓሻራ መርሃ ግብር ሥራዎች አማካኝነት በዘላቂ የግብርና ሥራ የታየው የኢትዮጵያ ርምጃ በጉባኤው ቀርቧል ሲሉም አስታውቀዋል።

በ’ኢትዮጵያ ታምርት’፣ በአግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች ጥምር የሥራ ፈጠራ ሥራ፣ በገቢ እድገት እና ጽናት የታዩት ኢንቨስትመንቶች በአለም የግብርና ዘርፍ የኢትዮጵያን ሚና አጠናክረውታል ነው ያሉት።

ረሃብን መዋጋት የጋራ ምላሽን ይሻል። ለዚህም ለምግብ ዋስትና የሚሆን የአለም አቀፍ ድጋፍ አቅርቦት፣ ድንበር ዘለል የሆነ የእውቀት ማካፈል ልምምድ፣ ለፍትሃዊ ተደራሽነት የሚረዳ የፖሊሲ መናበብ ብሎም ለሴቶች ትኩረት የሚሰጥ የአነስተኛ አርሶና አርብቶ አደሮች ድጋፍ ሥራ አስፈላጊ ነው ሲሉም አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም