ቀጥታ፡

ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ ያደርጋል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2017 (ኢዜአ)፡- በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 124 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ይህም አየር መንገዱ በተፋጠነ የስኬት ጉዞ ላይ እንደሚገኝ የሚያመላክት እርምጃ መሆኑንም ነው የገለጹት።

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ኤ350-1000 የመንገደኞች አውሮፕላን ከፈረንሳይ ቱሉስ ተነስቶ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል።

"Ethiopia Land of Origin" የሚል ስያሜ የተሰጠው ግዙፍ፣ ምቹና እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያለው ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ እንደሚያደርግም ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም