ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮ በጽህፈት ቤታችን ተቀብዬ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል ብለዋል።