ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 27/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን በማሸነፍዎ እና ወደ አሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ዳግም በመመለስዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡
የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር የኢትዮጵያ መንግሥት ከአዲሱ የአሜሪካ መንግሥት ጋር በቅርበት እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡