ቀጥታ፡

የፓን አፍሪካ የወጣቶች ፎረም ተሳታፊዎች በአልጄሪያ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 26/2017 (ኢዜአ)፦የአራተኛው የፓን አፍሪካ የወጣቶች ፎረም ተሳታፊዎች በአልጄሪያ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደዋል።

ፎረሙ በአልጄሪያ መካሄዱን ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና በፎረሙ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የወጣት መሪዎችን በማስተባበር በኦራን ኦሎምፒክ መንደር የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት እያከናወነች ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ በተመለከተ ለመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ ዛሬም እንደ ወትሮው ሁሉ ለአፍሪካ አንድነትና ሁለንተናዊ እድገት የመሪነት ሚናዋን መጫወቷን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ 55 ችግኞች በሁሉም የአፍሪካ አገራት ስም መተከሉን ከኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም