አምባሳደር ገነት ተሾመ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቀረቡ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ገነት ተሾመ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቀረቡ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 26/2017(ኢዜአ)፦ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ወዳጅነት እና የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላት ገልጸዋል።
ሩሲያ በቅርቡ በካዛን ከተማ 16ተኛውን የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ በስኬት ማጠናቀቋንና የሩሲያ-አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ስብሰባ ለማስተናገድ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ሩሲያ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰብዓዊ ጉዳዮች ከአጋር እና ወዳጅ አገራት ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ፑቲን መግለጻቸውን በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።