ቀጥታ፡

ፋኦ በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የመጣውን ተጨባጭ ለውጥ ለማስቀጠል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 26/2017 (ኢዜአ)፦የዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የመጣውን ተጨባጭ ለውጥ ለማስቀጠል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከፋኦ ዋና ኢኮኖሚስት ማክሲሞ ቴሬሮ ጋር በግብርናው ዘርፍ በቀጣይ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

ሚኒስትሩ ፋኦ የኢትዮጵያ መንግስት የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ በሚያደርገው ጥረት በገንዘብ፣በሙያ እና በአቅም ግንባታ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ድርጅቱ በቀጣይ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረግ ያለበትን ጉዳዮችንም በውይይቱ ወቅት አንስተዋል።

የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ኢኮኖሚስት ማክሲሞ ቴሬሮ በበኩላቸው በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ላለው ተጨባጭ ለውጥ እውቅና ሰጥተው ድርጅቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ በግብርናው ዘርፍ በትብብር በሚሰራባቸው ጉዳዮች ላይ በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም