የአክሱም ሐውልት እና የነገስታት መቃብር ሥፍራ የጥናትና ጥገና ማስጀመርያ ፕሮጀክት የሳይት ርክክብ ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የአክሱም ሐውልት እና የነገስታት መቃብር ሥፍራ የጥናትና ጥገና ማስጀመርያ ፕሮጀክት የሳይት ርክክብ ተካሄደ

አክሱም፤ ጥቅምት 26/2017 (ኢዜአ)፡- በሦስተኛው ረድፍ ላይ የሚገኘው የአክሱም ሐውልት እና የነገስታት መቃብር ሥፍራ የጥናትና ጥገና ማስጀመርያ ፕሮጀክት የሳይት ርክክብ ዛሬ በአክሱም ከተማ ተካሄዷል።
ርክክቡን ያደረጉት የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮና የጣሊያን ኩሮቺ ኤም ኤች ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ናቸው።
የጥናትና ጥገና የማስጀመሪያ ፕሮጀክት የሳይት ርክክብ የተፈፀመው 23 ሜትር ቁመት ያለው ሦስተኛው ረድፍ ላይ የሚገኘው ሐውልት ሲሆን፣ ክብደቱ 160 ቶን እንደሚመዝንም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ የቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በወቅቱ እንዳሉት፤ በዛሬው እለት የተካሄደው የማስጀመሪያ ፕሮጀክት የሳይት ርክክብ ስነ ስርዓት ቀደም ሲል የተደረገውን ጥናት ለመከለስና ወደ ስራ ለመግባት ታሳቢ ያደረገ ነው።