"ከረሀብ ነፃ ዓለም" ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
"ከረሀብ ነፃ ዓለም" ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 26/2017(ኢዜአ)፦ "ከረሀብ ነፃ ዓለም" ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በጉባዔው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የአቡዳቢ አልጋወራሽ ግርማዊ ሼህ ኻሊድ ቢን መሃመድ ቢን ዛይድ፣ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት፣ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተር ገርድ ሙለር ጥሪ የተደረገላቸው የጉባኤው ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
ከጥቅምት 26 እስከ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ዓለማቀፍ ጉባዔ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና ኢንቨስትመንት ለማጠናከር እየተሰራ ያለውን ስራ ለማጎልበት ያለመ ነው።
እንዲሁም የረሀብ ችግርን ለመፍታት የኢንቨስትመንትን አስፈላጊነትና የአለም አቀፍ ትብብር ጉዳይን ማሳደግ የጉባዔው አላማዎች ናቸው።
በዘርፉ እውቀትና ልምድ ያላቸው ተቋማትና ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
ጉባኤውን የኢትዮጵያ መንግስት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በጋራ አዘጋጅተውታል።
በአለም ላይ እያጋጠሙ ላሉ ተግዳሮቶች የመፍትሄ ሃሳብ የሚመላከትበት ጉባዔው መሆኑም ተመላክቷል።
ጉባኤው እንደ አገር አዳዲስ ኢንቨስትመንት ለመሳብ እንዲሁም የንግድ ግንኙነቶችን ለመፍጠር መልካም አጋጣሚ እንደሚሆን ይታመናል።
ኢትዮጵያ በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተገኙ ውጤቶች በተሞክሮ እንድምታቀርብ ይጠበቃል።