የዱባይ ፖሊስ ልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የዱባይ ፖሊስ ልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2017(ኢዜአ)፦ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተለያዩ ድጋፎችን የሚያደርጉ የዱባይ ፖሊስ ልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እ.ኤ.አ መጋቢት 2024 ከዱባይ ፖሊስ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ካሊፋ አልማሪ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል።
በውይይታቸው ወቅት ሌተናል ጀነራል ካሊፋ አልማሪ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በግብዓትና በስልጠና እንዲሁም የስማርት ፖሊስ ጣቢያ ለማቋቋም በገቡት ቃል መሠረት ድጋፍ የሚያደርግ ልዑካን ቡድን ኢትዮጵያ መግባቱ ተገልጿል።
ልዑካን ቡድኑ ከምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ነብዩ ዳኜ ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን ድጋፋ በሚከናወንበት ዕቅድ ላይ መክረዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ተቋሙ በለውጡ የፈጠራቸውን የቴክኖሎጂ አቅሞች ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።