ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ታሪካዊ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ታሪካዊ የሆነውን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አስታወቁ።

በሞሮኮ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናርዶስ አያሌው የሹመት ደብዳቤ ቅጂ ለሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡሪታ አቅርበዋል።

አምባሳደር ናርዶስ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ያላቸውን ለረጅም ጊዜ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን በሞሮኮ ኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም