በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የሰላም ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የሰላም ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2017(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች "ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሀሳብ የሰላም ኮንፍረንስ በመካሄድ ላይ ነው።
ጎንደር፣ ደባርቅ፣ መተማ፣ መርሳ፣ ደጀን፣ ቻግኒ፣ ማንኩሳ፣ ፈንድቃ፣ ሉማሜ እና ግንደወይን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች፣ የተለያዩ ዞኖች እና ወረዳዎች ላይ ውይይቶች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
በውይይቱ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ መምህራን፣ የየአካባቢው ነዋሪዎች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ የዞን እና ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።
የሰላም ኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች በወቅታዊ ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ እንደሚገኝ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።