ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2017(ኢዜአ)፦  የ2017 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ዛሬ ይጀመራል።

ቦሌ ክፍለ ከተማ ከአዳማ ከተማ ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

መርሃ ግብሩ ነገም ቀጥሎ ሲውል ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።

የመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።

በአምናው የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መቻል መካከል ሊደረግ የነበረው የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ንግድ ባንክ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ በሚያደርገው ተሳትፎ ምክንያት ለሌላ ጊዜ መሸጋገሩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም