ቀጥታ፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ሠላማዊት ካሳ የጎንደር የአፄ ፋሲል አብያተ-መንግስት ዕድሳትን ለመጎብኘት ጎንደር ከተማ ይገኛሉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2017(ኢዜአ)፡- በቱሪዝም ሚኒስትር ሠላማዊት ካሳ የተመራ የስራ ሃላፊዎች ቡድን የአፄ ፋሲል አብያተ-መንግስት የቅርስ ጥገናና ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለመጎብኘት ጎንደር ከተማ ይገኛል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጎንደር ከተማ ሲደርሱ የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው አፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ልዑካን ቡድኑ በጎንደር ከተማ በፌዴራል መንግስት እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን፣ የአፄ ፋሲል አብያተ-መንግስት የቅርስ ጥገናና የቱሪዝም መስህብ ቦታዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም