ኮሚሽኑ በክልሉ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በወላይታ ሶዶ እየመከረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኮሚሽኑ በክልሉ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በወላይታ ሶዶ እየመከረ ነው
ሶዶ ፤ ጥቅምት 22/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በወላይታ ሶዶ እየመከረ ነው።
በምክክር መድረኩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ የልዩ ልዩ ማህበራትና ተቋማት ወኪሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በመድረኩም በአጠቃላይ ከ1 ሺህ 800 በላይ የሚሆኑ ወኪሎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
የምክክር መድረኩ ታሳታፊዎች በወከሏቸው አካላት የተነሱ አጀንዳዎች ላይ ከመከሩ በኋላ በመረጧቸው ተወካዮቻቸው አማካኝነት አጀንዳዎቻቸውን ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እንደሚያስረክቡ ተመላክቷል።