የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች የበለጠ ለማጠናከር በጠንካራ ቅንጅታዊ አሠራር መንቀሳቀስ ይገባል -ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች የበለጠ ለማጠናከር በጠንካራ ቅንጅታዊ አሠራር መንቀሳቀስ ይገባል -ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች የበለጠ ለማጠናከር በጠንካራ ቅንጅታዊ አሠራር መንቀሳቀስ ይገባል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ ይሄንን ያሉት በመላው ዓለም ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤቶች ኃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።
በዚሁ ወቅትም የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች የበለጠ ለማጠናከር በጠንካራ ቅንጅታዊ አሠራር መንቀሳቀስ እንደሚገባ ሚኒስትሩ ማሳሰባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዶክተር ጌዲዮን በውይይቱ ላይ እንዳሳሰቡት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ወቅታዊውን የዓለም ጂኦ-ፖለቲካ አካሄድ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው።