በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና መቀሌ 70 እንደርታን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21/2017(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና መቀሌ 70 እንደርታን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አጥቂው አንተነህ ተፈራ በ57ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት በ60ኛው ደቂቃ በጨዋታ ያስቆጠራቸው ግቦች ቡናማዎቹን አሸናፊ አድርጓል።

ኢትዮጵያ ቡና በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ መቀሌ 70 እንደርታ በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ቀን ላይ በተደረገው የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ መቻል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 1 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም