ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ(5G) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 21/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ(5G) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው።

የአምስተኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ(5G) ፈጣኑ የኔትወርክ አገልግሎት መሆኑን በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

ቴክኖሎጂው የዕለት ከዕለት ስራን ለማቀላጠፍና አጠቃላይ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት ሚናው ከፍተኛ እንደሆነም ተጠቁሟል።

ከዓመታት በፊት ይፋ ተደርጎ እስከአሁን ስራ ላይ ካለው 4ኛው ትውልድ(4G) ቴክኖሎጂ ጋር ሲነፃፀርም ከ100 እጥፍ በላይ ፍጥነት እንዳለው ተገልጿል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የክልሉ ምክር ቤት አፌ-ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

አምስተኛው ትውልድ የኔትዎርክ አገልግሎት(5G) አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ እና ባህርዳርን ጨምሮ በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም