አቶ አረጋ ከበደ ከባሕር ዳር ከተማ ባለሃብቶች ጋር ውይይት አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
አቶ አረጋ ከበደ ከባሕር ዳር ከተማ ባለሃብቶች ጋር ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21/2017(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ውይይቶች ተካሂደዋል።
በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ መልዕክት በባሕር ዳር ከተማ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ርእሰ መሥተዳድሩን ጨምሮ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ኀላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግሥቴ፣ የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች መገኘታቸውን የአሚኮ ዘገባ ያመላክታል።