ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል የሚለው መረጃ ሃሰት ነው- አየር መንገዱ

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2017 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሃሰት መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ በዛሬው ዕለት አንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገጾች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል የሚል መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ተመልክተናል ብሏል።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራን አየር ክልል እንዲጠቀም ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ፈቃድ የተሰጠውና የኤርትራ አየር ክልልን ለመደበኛ በረራ እየተጠቀመ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ስለሆነም በማህበራዊ ትስስር ገጾች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሃሰት መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም