ምክር ቤቱ የቀረበለትን ሞሽን አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ የቀረበለትን ሞሽን አጸደቀ

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2017(ኢዜአ)፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 27 ቀን 2017 በፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የቀረበውን የ2017 የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ ሞሽን አጽድቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብስባውን ዛሬ አካሂዷል፡፡
በፕሬዚዳንቱ የቀረበውን ሞሽን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያና ምላሽ ተሠጥቶባቸዋል፡፡