የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በደሴ እና ጎንደር ከተሞች የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

ደሴ/ጎንደር ፤ ጥቅምት 20/2017(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን(ዶ/ር) እና ሌሎች የክልሉ አመራሮችና የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በከተማው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝቱም የደሴ ከተማ አስተዳደር የኦን ላይን አገልግሎት አሰጣጥ በይፋ የተጀመረ ሲሆን በህብረተሰቡ የታደሰው የከተማ አስተዳደሩ ህንጻ እና ሌሎች የልማት ስራዎች ተካተዋል።

በጉብኝቱ ላይ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ ከደሴ ከተማ የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ወጣቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች በከተማው ነዋሪዎች፣ በክልልና በከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እየተጎበኙ ነው።


 

ጉብኝቱም በከተማው የኮሪደር ልማት ሥራዎች፣ የከተማው የኢንቨስትመንት ማስፋፋትና የመሰረተ ልማት ሥራዎችን እንደተካተቱ ተመላክቷል።

እየተጎበኙ ካሉ የልማት ሥራዎች መካከል የዓባይ ጋርመንት ፋብሪካ እና በከተማው የሌማት ትሩፋት እንቅስቀሴ ጨምሮ የፒያሳ ኮሪደር ልማትና የአጼ ፋሲል አብያተ መንግስት የቅርስ ጥገና ሥራዎች ይገኙበታል።

በጉብኝቱ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰውን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም