ቀጥታ፡

የዳያስፖራው ማህበረሰብ በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ አለበት - ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) )

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19/2017(ኢዜአ)፦ የዳያስፖራው ማህበረሰብ በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) አመለከቱ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከፅናት ለኢትዮጵያ እና ከሰላም እና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበራት የተሰባሰቡ አጀንዳዎችን ከማህበራቱ ተወካዮች ዛሬ ተረክቧል።

መቀመጫቸውን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በማድረግ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውኑ የቆዩት ማህበራት በተወካዮቻቸው አማካኝነት ሀገራዊ መግባባት ሊደረግባቸው ይገባል ብለው ያመኑባቸውን የምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረክበዋል።


 

የማህበራቱ ተወካዮች በኮሚሽኑ ፅህፈት ቤት በነበራቸው ውይይት በቀጣይም ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ በመስራት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የምክክር ሂደት ለመደገፍ ያላቸውን ፈቃደኝነት ገልጸዋል።

ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) የማህበራቱን የእስከ አሁን እንቅስቃሴ አድንቀው የዳያስፖራው ማህበረሰብም በተለያዩ መንገዶች አጀንዳዎቻቸውን በመስጠት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ መጠየቃቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም