ቀጥታ፡

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ቤይጂንግ (ቻይና) ገባ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2017(ኢዜአ)፦ በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ቤይጂንግ (ቻይና) ገብቷል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራው የልኡካን ቡድን ቤይጂንግ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ሲደርስ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው አቀባበል አድርገውለታል።


 

የልዑካን ቡድኑ ጉዞ የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ ሲሆን በቆይታውም የሁለትዮሽ ውይይቶች፣ የተሞክሮ ልውውጦች እና የመስክ ጉብኝቶችን እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በተለይም የወደፊት የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቶችን የሚያጠናክሩ ስትራቴጂያዊ አጋርነት መመስረትን ዓላማ ያደረገ ቆይታ ያደርጋል ተብሎም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም