ቀጥታ፡

የከተማዋን ሰላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የልማት ስራዎች በጥራትና በፍጥነት በመከናወን ላይ ናቸው- አቶ ጎሹ እንዳላማው

ባሕርዳር ፤ ጥቅምት 17/2017 (ኢዜአ)፡- የባህር ዳር ከተማን ሰላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የልማት ስራዎችን በጥራትና ፍጥነት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።

በባህር ዳር ከተማ "የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሃሳብ ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ የሰሜን ጎጃምና ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር አመራር አባላት በከተማዋ እየተገነቡ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን እየጎበኙ ነው።


 

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እንደገለጹት፤ የባህር ዳር ከተማን ሰላም የማስጠበቅና ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት የማከናወን ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በከተማዋ የከንቲባ ጽሕፈት ቤትን ለስራ ምቹና ማራኪ ከማድረግ በተጨማሪ ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ የአስፋልት መንገድ ግንባታዎች እየተከናወኑ እንደሆነም ገልፀዋል።

ከተማዋን ዘመናዊና ተመራጭ ከተማ ለማድረግ ተፈጥሮ ያደላት በመሆኑ የተፈጥሮ ፀጋዋን የማጉላት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ሂደት፣ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት እድሳት፣ ጣና ማሪን ፕሮጀክት ግንባታና የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴዎች የጉብኝቱ አካል ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም