የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዳማ፤ጥቅምት 16/2017(ኢዜአ)፦ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዘጋጅነት በ19ኛው የኢትዮጵያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ላይ ያተኮረ መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የመንግስት ግንኙነት፣ የዴሞክራሲ አንድነትና የህገ መንግስት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ፀሃፊ ወይዘሮ ባንቺይርጋ መለሰ እንዲሁም የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤት የጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ''ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሔራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚከበርም ተገልጿል።