ቀጥታ፡

117ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2017 (ኢዜአ)፦117ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን "በፈተናዎች እየተገነባ የመጣ ሠራዊት" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።

የመከላከያ ሰራዊት ቀን በመከላከያ ሰራዊት ዋና መምሪያ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።

በመርሀ ግብሩ ላይ የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የሰራዊቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በመስዋዕትነት ያስከበረው መከላከያ ሠራዊት ዘመናዊ ወታደራዊ መዋቅር እና የጦር ሠራዊት ሆኖ ከተዋቀረ ዛሬ 117ኛ ዓመቱን መያዙም በአከባበሩ ላይ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም