ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በአንካራ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት አወገዘች

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 14/2017 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በተርክዬ አንካራ ከተማ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት እንደምታወግዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ በተርክዬ አንካራ በሚገኘው የተርክሽ ኤርስፔስ ኢንዱትስትሪ ላይ በተፈፀመው የሽብር ጥቃት ምክንያት በሞቱ ሰዎች ማዘኗን ገልጿል።

በጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ የሟች ቤተሰቦች፣ ለተርክዬ ህዝብ እና መንግስት መፅናናትንም ተመኝቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት ያወግዛል ያለው መግለጫው፤ ተርክዬ አሸባሪዎችን ለመዋጋት በምታደርገው ጥረት የኢትዮጵያ መንግስት ከጎኗ እንደሚቆም አረጋግጧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም