ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር እየተወያዩ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር እየተወያዩ ነው
ሆሳዕና፤ ጥቅምት 14/2017(ኢዜአ)፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር በሆሳዕና ከተማ እየተወያዩ ነው።
መድረኩ በክልሉ በኤሌክትሪክ አገልግሎት ዘርፍ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በተቀናጀ መንገድ በዘላቂነት ለመፍታት በሚያግዙ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የኃይል መቆራረጥ ማስቀረት የሚያስችሉ ጉዳዮች ተነስተው በጋራ እንደሚመከርባቸው ተመላክቷል።
እንዲሁም ክፍያ ተፈጽሞ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በተገቢው መንገድ ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ችግሩን ከመለየት ባለፈ በቀጣይ ማህበረሰቡን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ የመፍትሄ ሀሳቦች በመድረኩ እንደሚመላከቱም ተገልጿል።
የኤሌክትሪክ አገልግሎት በሚፈለገው መጠን እንዳይዳረስ እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን በተቀናጀ መንገድ በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ የጋራ መግባባት ላይ መድረስም የመድረኩ ትኩረት ነው።
በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላን ጨምሮ የአገልግሎቱ ሥራ ሃላፊዎችና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።