ቀጥታ፡

ኢትዮጵያውያን ሰው ልብ ውስጥ መቆየት የሚችሉና የሚደነቅ ማንነት አላቸው - የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሰፔ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያውያን ሰው ልብ ውስጥ መቆየት የሚችሉና የሚደነቅ ማንነት አላቸው ሲሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) ፕሬዚደንት ፓትሪስ ሞትሴፔ (ዶ/ር) ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ ማምሻውን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ ለፕሬዚደንቱ ሽኝት አድርገዋል።


 

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ መንግስት በተደረገላቸው አቀባበል እና መስተንግዶ ምስጋና አቅርበዋል።

አዲስ አበባ በነበረኝ ቆይታ ኢትዮጵያውያን ውብ የሆነ ባህል ያላቸው፣ እንግዳ ወዳድና አክባሪ እንደሆኑ አይቻለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ 46ኛውን የካፍ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ መምጣታቸውንና ጉባዔው በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን መግለጻቸውን ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም