ቀጥታ፡

የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች የሚያ​​​​​​​ስተዋውቅ ሴሚናር በጃፓን ተካሄደ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2017 (ኢዜአ)፦ በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት የኢትዮጵያን የቱሪስት መስህቦች የማስተዋወቂያ የቱሪዝም መድረክ ተካሄዷል።

በጃፓን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዳባ ደበሌ ስለ ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብት እና የቱሪዝም መዳረሻዎች ገለጻ አድርገዋል።


 

አምባሳደሩ ጃፓናዊያንም በኢትዮጵያ ባሉ የቱሪዝም እና ሌሎች የኢንቨስትመንትና እና የቢዝነስ አማራጮች ላይ እንዲሰማሩ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቸኛው አፍሪካን ከጃፓን በቀጥታ የሚያገናኝ አየር መንገድ በመሆኑ ለጃፓናዊያን ኢትዮጵያን እንዲሁም አፍሪካን ለመጎብኘት መልካም አጋጣሚ መሆኑንም መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም