የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ ያደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2017(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ያደረሰውን ጉዳት በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ የእሳት ቃጠሎ የደረሰበትን ሕንፃ ግማሽ አካልን ከአደጋው ማትረፍ ተችሏል።


 

የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና የፀጥታ አካላት በተቀናጀ መንገድ አደጋውን ለመቆጣጠር እና አደጋው እንዳይዛመት ያደረጉት የተቀናጀ ርብርብ የሚመሰገን መሆኑንም ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በተከሰተው የእሳት አደጋ የንብረት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በትኩረት እንደሚሠራ አቶ ሞገስ መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም