ቀጥታ፡

የካፍ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 11/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።

በስብስባው ላይ የካፍ ፕሬዝዳንት እና የኮሚቴው ሰብሳቢ ፓትሪስ ሞትሴፔ እና ሌሎች የኮሚቴው አባላት ተገኝተዋል።

የካፍ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 23 አባላት ያሉት ነው።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ የኮሚቴው አባል ናቸው።

46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ጠቅላላ ጉባዔ ነገ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም