ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትስፔ አደይ አበባ ስታድየምን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 11/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የአደይ አበባ ስታድየምን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔን ጨምሮ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ጥያቄ ማቅረቧን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝም የናይጄሪያ የቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ዳንኤል አሞካቺና ንዋንኩ ካኑ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተመርጠው ጥረቶች መጀመራቸውንም መጥቀሳቸው እንዲሁ።

46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ጠቅላላ ጉባዔ ነገ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም