8ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 11/2017(ኢዜአ)፦8ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ሕብረት የተባበሩትና መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የትብብር ምክክር መድረክ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በምክክሩ ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የተቋማቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ የአፍሪካ ሕብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትብብር ማዕቀፎች አፈጻጸም እንደሚገመገም ኢዜአ ከሕብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሁለቱ ተቋማት ሰላም እና ደህንነትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸው ትብብር ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ምክክሩን አስመልክቶ ከሰዓት በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሏል።

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ የስራ ቆይታ ለማድረግ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

ዋና ፀሐፊው እድሳት የተደረገለትን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ሕንጻን ይመርቃሉ ተብሎም ይጠበቃል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም