የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 11/2017(ኢዜአ)፦የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ የስራ ቆይታ ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዋና ፀሀፊው ቦሌ ዓለማቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና የተመድ ም/ዋና ፀሀፊ አሚና መሀመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በዓመታዊው የተመድ አፍሪካ ህብረት ኃላፊዎች ስብሰባ ላይ ይካፈላሉ፡፡
አንቶኒዮ ጉተሬዝ ዳግም የታደሰውን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ህንፃ ይመርቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።