በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመገኘት እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርምና የተቋም ግንባታ ስራዎችን ጎብኝተናል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2017(ኢዜአ)- በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመገኘት እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርምና የተቋም ግንባታ ስራዎችን ጎብኝተናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በጉብኝታቸው፥ የከተማዋን ቁመና የሚመጥን በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ እና በሎጀስቲክ የተደራጀ፤ ከነዋሪዎች ጋር በቅርበት የሚሰራ የፖሊስ ተቋም ለማደራጀት የተጀመረው ስራ ዉጤታማ መሆኑን መመልከታቸውን ጠቁመዋል ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ እስካሁን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለተገኘው ውጤት አመስግነዋል።

በቀጣይም የሪፎርም ስራው እስከታችኛው መዋቅር እንዲደርስ እና የአገልጋይ ፖሊስ ዲሲፕሊን እየተጠናከረ እንዲሄድ የተጀመረውን ስራ የምንቀጥል መሆኑን ማሳወቅ እወዳለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም